ኢትዮጵያ በጂኦተርማል ኃይል ዘርፍ ያላት እምቅ ሀብት በመንግሰትም ይሁን በግሉ ዘርፍ ጥቅም ላይ ሲውል ለሀገራችን የሀይል አቅርቦት ተጨማሪ አቅም ይሆናል። ባለፉት አመታት በአርሲ ኢተያ የጂኦተርማል ኃይል ለማምረት አንቅስቃሴ ላይ የቆየው TM Geothermal operation PLC.(TMGO) በመጀመሪያው ምእራፍ ላይ 50 ሜ.ዋት ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን ኩባንያው በዛሬው እለት የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ግንባታውን ለማከናወን ከMitsubishi Corporation እና SEPCOlll Electric […]
የጨው ምርትና ግብይት ላይ ያተኮረ እንዲሁም የምርት ሂደቱ በዜጎች ጤና ላይ ባለው ተጽእኖ ዙሪያ የንግድ ሚኒስቴር እና የማዕድን ሚኒስቴር ባለሙያዎች በትብብር ጥናት አድርገዋል፤ባለሙያዎቹ በርካታ ግብአቶችንና ግኝቶችን ለይተዋል:: በዛሬው እለትም ከንግድ ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ጋር አፋር ሰመራ ተገኝተን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የጥናቱ ሙሉ አውድ ላይ መግባባት […]
የግንባታ ግብዓቶችን በመጠንና በጥራት እንዲቀርቡ ማድረግ ፣ የወጭ ንግድ ምርቶችን በጥራት እና ብዛት መጨመር ላይ የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም አጠቃላይ የማዕድን ሀብታችን ጥቅም ላይ እየዋለበት ያለበትን መንገድ የገመገምን ሲሆን አፈፃፀሙም መልካም የሚባልና ከፍተኛ ተስፋ የሚታይበት ነው:: ቀጣይ ጊዜያችን የማዕድን ምርታችን በመጠንና ጥራት አሳድገን ለአለም ገበያ የምናቀርብበትና ለሀገራችን የውጪ ምንዛሪ ማገር የምንሆንበት እንዲሁም ከውጭ የሚናስገባቸውን ምርቶችም በሂደት […]
የጣልያን አምባሳደር Agostino Palese ከማዕድን ሚኒስቴር ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋራ ባካሄዱት ውይይት የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡ ድጋፉ በአሶሳ ለሚገነባው የዕምነበረድ ፓርክ እንዲሁም የአሶሳ የዕምነበረድ ማሰልጠኛን ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡በተጨማሪም ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የዕምነበረድ ሙያ ሰልጣኞች ወደ ጣልያን በመሄድ ስልጠና የሚያገኙ ይሆናል፡፡የተማረ የሰው ኃይላችንን ለማሳደግ የምንሰራው ስራም በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል፡፡
በአሸባሪው የህዋሃት ቡድን ምክንያት በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ ለክልሉ መንግስት አስረክቧል፡፡ ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ ሲሆኑ የአሸባሪው የህዋሃት ቡድን ባደረሰብን ወረራና ግፍ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የክልላችን ህዝቦች መልሶ ለማቋቋም እያደረግን ላለው ጥረት የሚያግዝ በመሆኑ ምስጋናችን […]
በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ጊዜውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ የሚያስችል የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት ከአምራቾች በቀጥታ እንዲያገኙ ተወሰኗል፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር ከመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ለመስኖ ልማት ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን የሲሚንቶ አቅርቦት ከአምራቾች በቀጥታ እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡ ለግንባታ የሲሚንቶ አቅርቦት ወሳኝ በመሆኑ በደላሎች አማካኝነት የሚቀርበውን የሲሚንቶ ምርት በቀጥታ እንዲያገኙ በጋራና በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል፡፡ በዚሁ መሰረትም ከመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር […]
የማዕድን ሚኒስቴር በሐገሪቱ የሚገኘውን የማዕድን ሃብት በሚገባ በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል፡፡ ዘርፉ ከፍተኛ የሆነ ኢንቨስትመንት የመሳብ አቅም ያለው ሲሆን በመንግስትም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ የማዕድን ሃብት ክምችት በየክልሎቹ የሚገኝ በመሆኑ ከዘርፉ አመራሮች ጋር በቅንጅት መስራትና መደገፍ ይገባል፡፡ ክልሎችም ሃብቱን በሚገባ ማስተዋወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚገኘውን የማዕድን ሃብት ለማስተዋወቅ ያለመ ኤግዚቢሽንና ፎረም […]
ኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጣቸው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ከሚገኙ ክምችቶች የድንጋይ ከሰል ማዕድንን አዋጭ በሆነ መንገድ በከፍተኛ ደረጃ በማምረት አና በማበልጸግ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት ለማቅረብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት ነው፡:ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስትር ክቡር ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስኪያዎች ተፈራርመዋል፡፡ ኢቲ የማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር እና ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግስ ኩባንያዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ሰን ማይንኒግና […]
የማዕድን ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሐገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ለውይይቱ “የድህረ ጦርነት መዛነፎችና እርምቶች” በሚል ርዕስ በድህረ ጦርነት ያሉ ተስፋዎችና ስጋቶች ከክልሎች ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ከብሔራዊ መግባባትና ከሀገር ግንባታ አንጻር የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡ ሰራተኞቻች ገንቢ የሆነ፣ ለሀገር ግንባታ ፋይዳው የጎላ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ […]
የማዕድን ሚኒስቴር የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር ግምገማና ውይይት ተካሄዷል፡፡ በዘርፉ ባለፉት ሶስት ወራት ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ የዘርፉ የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም በማዕድን ምርት አቅርቦት በከፊል የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡ በኢንዱስትሪ ግብዓቶች ምርት በሲሚንቶ ምርትና አቅርቦት የነበረው ችግር በመፍታት በቀን እየተመረተ ያለውን 160,000 ሺ ቶን ወደ 240,000ሺ […]