ለመስኖ ልማት ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የሚቀርበውን የሲሚንቶ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ፡፡

በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ጊዜውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ የሚያስችል የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት ከአምራቾች በቀጥታ እንዲያገኙ ተወሰኗል፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር ከመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ለመስኖ ልማት ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን የሲሚንቶ አቅርቦት ከአምራቾች በቀጥታ እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡ ለግንባታ የሲሚንቶ አቅርቦት ወሳኝ በመሆኑ በደላሎች አማካኝነት የሚቀርበውን የሲሚንቶ ምርት በቀጥታ እንዲያገኙ በጋራና በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል፡፡ በዚሁ መሰረትም ከመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እንሰራለን ሲሉ የማዕድን ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጅነር አይሻ መሃመድ በበኩላቸው የመስኖ ስራ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በመሆኑ እና ግድቦችን በተቀመጠላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ወደ ስራ ለማስገባት እያጋጠመ ያለውን የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ኮንትራክተሮቻችን በቀጥታ ከሲሚንቶ አምራቾች የሚገዙበትን አሰራር በመዘርጋቱ መልካም ነው፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

Leave A Comment

MoM