የማዕድን ዘርፍን ዋና የዕድገት ምንጭ ለማድረግ በቅንጅት ይሰራል ተባለ፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር ግምገማና ውይይት ተካሄዷል፡፡ በዘርፉ ባለፉት ሶስት ወራት ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የዘርፉ የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም በማዕድን ምርት አቅርቦት በከፊል የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡ በኢንዱስትሪ ግብዓቶች ምርት በሲሚንቶ ምርትና አቅርቦት የነበረው ችግር በመፍታት በቀን እየተመረተ ያለውን 160,000 ሺ ቶን ወደ 240,000ሺ ቶን ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ምርቱ ከነበረበት የ900 ብር ዋጋም ወደ 450 ብር በኩንታል ማውረድ ተችሏል፡፡ ከውጭ የሚገባውን የድንጋይ ከሰል ምርት ሙሉ በሙሉ በሐገር ውስጥ ለማምረት የምርትና ፕሮሰሲንግ ፈቃዶችን ለኩባንያዎች ለመስጠት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)‹‹መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በሚገባ በመጠቀም የማዕድን ዘርፍን ዋነኛ የእድገት ምንጭ ለማድረግ በጋራ እንሰራለን፤ ከውጭ የሚገባውን የድንጋይ ከሰል በሐገር ውስጥ ለመተካት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያደረገውን ጥረት በአስቸኳይ ወደ ምርት ለማስገባትም መንግስት ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል›› ብለዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ በማዕድን ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች የተሻሉ ቢሆኑም የበለጠ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል:: የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የሰጡትን ገንቢ አስያየትና ሃሳብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዘርፉ የመቶ ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውም በውይይቱ ተጠቅሷል፡፡ የሁለቱም ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ሚኒስትሮችና ሚንስትር ዴኤታዎች የተገኙ ሲሆን ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችም ላይ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡

Leave A Comment

MoM