በአሸባሪው የህዋሃት ቡድን ምክንያት በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ ለክልሉ መንግስት አስረክቧል፡፡ ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ ሲሆኑ የአሸባሪው የህዋሃት ቡድን ባደረሰብን ወረራና ግፍ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የክልላችን ህዝቦች መልሶ ለማቋቋም እያደረግን ላለው ጥረት የሚያግዝ በመሆኑ ምስጋናችን […]
የማዕድን ሚኒስቴር የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር ግምገማና ውይይት ተካሄዷል፡፡ በዘርፉ ባለፉት ሶስት ወራት ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ የዘርፉ የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም በማዕድን ምርት አቅርቦት በከፊል የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡ በኢንዱስትሪ ግብዓቶች ምርት በሲሚንቶ ምርትና አቅርቦት የነበረው ችግር በመፍታት በቀን እየተመረተ ያለውን 160,000 ሺ ቶን ወደ 240,000ሺ […]
እድገትን መመኘት ብቻውን በቂ አይሆንም ፤ ያቀድነውን ለመፈፀም መትጋት ይጠበቃል። የማዕድን ሚኒስቴር የተሰጠው ኃላፊነትን ለመፈፀም ቅንጅትን ዋነኛ ማዕከሉ አድርጓል። በቅንጅት የማዕድን ወጪ ንግድን እናሳድጋለን ፤ከዚህ በሻገርም ከውጪ የሚገቡ የማዕድን ምርቶችን በሀገር ወስጥ ለማምረት ትክክለኛው መንገድ ላይ እንገኛለን። ይህ ሁሉ ሀሳብ ያለ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሰራተኞች የሚሳካ አይደለም፤ህልማችን ከሰራተኞቻችን ጋር በቅንጅት የምናሳካው ነው። ባለፉት ሁለት ቀናት የሚኒስቴር […]
ከ6 የማዕድን ኩባንያዎች ጋር የምርት ፈቃድ ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስኪያጆች ተፈራርመዋል፡፡ ኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጣቸው የማዕድን ፍለጋውን አጠናቀውና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት ነው፡፡ ኩርሙክ ጎልድ ማይን ፣ኢትኖ ማይኒንግ እና ኦሮሚያ ማይኒንግ ኩባንያዎች የወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡ አሊ ሀሚል ካሐዲም የብሮሚን እና ክሎሪን ምርት ፈቃድ ወስዷል፡፡ […]
የሚሰሩ ጠንካራ እጆች ሁሌም ድጋፍ ይገባቸዋል።የባህላዊ እና አነስተኛ ወርቅ አምራቾቻችን ለሀገራችን የማዕድን ክፍለ ኢኮኖሚ ዋልታ ሆነው ዘመናትን እያሻገሩን ይገኛሉ። እነሱን በተለያየ መንገድ መደገፍ ፣ከትከሻቸው ላይ ጫናዎችን ማቃለል ከእኛ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው። የክልሎቻችን ርእሰ መስተዳድሮች በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ ለሚያቀርቡት አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረውን የሮያሊቲ ክፍያን ሙሉ በሙሉ አንስተዋል። ይህ እርምጃ ለባህላዊ የማዕድን ምርት እንደሀገር […]
በማዕድን ዘርፍ ህግና ስርአትን ማስከበርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ስርአት ማስያዝ የቀጣዩ አመት እቅድ ስኬት ዋነኛው ግብአት የሚሆን ነው።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታና የቁጥጥር ስራዎችን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። ስምምነቱም ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባ ነው። በስምምነቱ መሰረትም በድንበር አካባቢዎች ህገወጥ የወርቅ ዝውውርና ለመከላከል ጠንካራ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ወርቅ ወይም ሌሎች ማዕድናት በሚወጣባቸው አካባቢዎች […]
የኖርዌዩ አኮቦ ሚኔራልስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሰገሌ የወርቅ ማዕድን ቦታ ወርቅ እና አብረው የሚገኙ ማዕድናትን ለማውጣት የሚያስችለውን ፈቃድ አግኝቶ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ የአኮቦ ሚኔራልስ ኩባንያ ኃላፊ ጆርገን ኤቭጄን÷ኩባንያቸው በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ ሲወስን እንዴት ግጭት በተቀሰቀሰበት የጦር ቀጠና ትሄዳላችሁ የሚሉ ጥያቄዎች ከሌሎች አቻ ኩባንያዎች ሲቀርብላቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ከኩባንያዎቹ የማስጠንቀቂያ አስተያየቶች በተጨማሪ አዲስ አበባ በአሸባሪው እጅ ወድቃለች […]
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት (2013) ከማዕድን ምርቶቻችን 681 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝተናል። ይህም ባለፋት ዓመታት ከተገኘው የውጭ ምንዛሪ ትልቁ በመሆን ተመዝግቧል። በቀጣይ ዓመትም ከዘርፉ ከዚህ የተሻለ ለማግኘት እቅድ አስቀምጠን ወደ ተግባር ገብተናል። ያሰብነውን ሳናሳካ እረፍት የለንም! ያሰብነውን እንደምናሳካና የማአድን ሀብታችንም የኢኮኖሚያችን ዋልታ እንደሚሆን እየሄድንበት ያለው መንገድ የሚታይ ምስክር ነው።
ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት በICL ((Israel Chemical Limited) በተባለ የፖታሽ ማዕድን አውጪ ኩባንያ የተመሰረትባትን የ300 ሚሊዮን ዶላር ክስ በትናንትናው ዕለት በአሸናፊነት ተወጥታለች። ክሱ የቀረበበትና ይግባኝ የማይባልበትን ፍርድ የሰጠው በሄግ ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት (Permanent Court of Arbitration) ነው በክርክሩ ሂደት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳታፊ ለነበራችሁ ሁሉ፤ በተለይም የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስቴርና […]
በተያዘው አመትም በታሪካችን ከፍተኛውን ገቢ ከማአድን ዘርፍ አግኝተናል። በ11 ወር ብቻ ከ668 ሚሊዮን ዶላር በላይ አግኝተናል። በቀጣይ አመትም ከዘርፉ 1.5 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት እቅድ አስቀምጠን ከክልሎች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል። እቅዳችን እንዲሳካም በዘርፉ እየታዩ ያሉ ችግሮችን ማስተካከል ከኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው።በማዕድን ማውጫ አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በተመለከተ በሰላም ሚኒስቴር በኩል መፍትሄ የሚያገኝ መሆኑን መግባባት ላይ […]