የማዕድን ሚኒስቴር ለአማራ ክልል 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

በአሸባሪው የህዋሃት ቡድን ምክንያት በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ ለክልሉ መንግስት አስረክቧል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ ሲሆኑ የአሸባሪው የህዋሃት ቡድን ባደረሰብን ወረራና ግፍ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የክልላችን ህዝቦች መልሶ ለማቋቋም እያደረግን ላለው ጥረት የሚያግዝ በመሆኑ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡ ሌሎች የፌዴራል ተቋማትም ይህንን አርዓያ በመከተል ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያችን እናቀርባለን ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሌ አበበ በበኩላቸው የማዕድን ሚኒስቴር በክልሉ የማዕድን ሃብትን ለማልማት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ለተደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Leave A Comment

MoM