ለ8 ኩባንያዎች የድንጋይ ከሰል ምርት ፈቃድ ተሰጠ፡፡

ኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጣቸው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ከሚገኙ ክምችቶች የድንጋይ ከሰል ማዕድንን አዋጭ በሆነ መንገድ በከፍተኛ ደረጃ በማምረት አና በማበልጸግ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት ለማቅረብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት ነው፡:ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስትር ክቡር ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስኪያዎች ተፈራርመዋል፡፡

ኢቲ የማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር እና ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግስ ኩባንያዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ሰን ማይንኒግና ትሬዲንግ ፒ ኤል ሲ ኩባንያ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ ኦሮሚያ ማይኒንግ አክሲዮን ማኅበር፣ ናሽናል ማይኒንግ ኮርፖሬሽን እና ሪያልማይን ትሬዲንግ ፒ ኤል ሲ ኩባንያዎች በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ሻቃና ልጆቹ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ኤልኔት ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምርት ፈቃድ ወስደዋል፡፡

ኩባንያዎቹ 6 ቢሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ካፒታል አስመዝግበዋል፡፡ የድንጋይ ከሰል ፕሮጀክት በዘርፉ ከሚከናወኑ አጠቃላይ የማዕድን ዘርፉን የማልማት፣ የማዕድናትን ሀገራዊ ምርት የማሳደግ፣ በዘርፉ ሰፊ የስራ ዕድል የመፍጠር፣ አምራች ሀገራዊ ባለሀብቱን በማበረታታት በዘርፉ ዕሴት እንዲጨምሩ፣ ወጣቶች ከባለሀብቶች ጋር በመስራት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል ይፈጥራል፡፡

Leave A Comment

MoM