ኢትዮጵያ በጂኦተርማል ኃይል ዘርፍ ያላትን እምቅ ሀብት ለማልማት ይሰራል!

ኢትዮጵያ በጂኦተርማል ኃይል ዘርፍ ያላት እምቅ ሀብት በመንግሰትም ይሁን በግሉ ዘርፍ ጥቅም ላይ ሲውል ለሀገራችን የሀይል አቅርቦት ተጨማሪ አቅም ይሆናል።

ባለፉት አመታት በአርሲ ኢተያ የጂኦተርማል ኃይል ለማምረት አንቅስቃሴ ላይ የቆየው TM Geothermal operation PLC.(TMGO) በመጀመሪያው ምእራፍ ላይ 50 ሜ.ዋት ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን ኩባንያው በዛሬው እለት የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ግንባታውን ለማከናወን ከMitsubishi Corporation እና SEPCOlll Electric Power Construction co., ltd ጋር የ 100 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኃይል የማመንጫ ግንባታው በሁለት አመት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ኃይል ማመንጨቱ ይገባል።

Leave A Comment

MoM