የማዕድን ኤግዚቢሽን እና ፎረም በየክልሎቹ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር በሐገሪቱ የሚገኘውን የማዕድን ሃብት በሚገባ በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል፡፡ ዘርፉ ከፍተኛ የሆነ ኢንቨስትመንት የመሳብ አቅም ያለው ሲሆን በመንግስትም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

የማዕድን ሃብት ክምችት በየክልሎቹ የሚገኝ በመሆኑ ከዘርፉ አመራሮች ጋር በቅንጅት መስራትና መደገፍ ይገባል፡፡ ክልሎችም ሃብቱን በሚገባ ማስተዋወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚገኘውን የማዕድን ሃብት ለማስተዋወቅ ያለመ ኤግዚቢሽንና ፎረም “የማዕድን ሃብታችን ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል አዘጋጅቷል፡፡ ዘርፉን ተቀናጅቶ በማልማት የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ ፋይዳው ከፍተኛ ነው፡፡ ኤግዚቪሽንና ፎረም መካሄዱ አመራሩ የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ ሲሆን የሚያጋጥሙ ችግችንም ለመፍታት ያስችላ፡፡

በቀጣይም ሌሎች ክልሎች የማዕድን ኤግዚቪሽንና ፎረም በማዘጋጀት ዘርፉን የማስተዋወቅ ስራ መቀጠል እንዳለበት ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡

Leave A Comment

MoM