Category: Logistics

በኢትዮጵያ የጣሊያን አማባሳደር የ20ሚሊየን ብር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገቡ

የጣልያን አምባሳደር Agostino Palese ከማዕድን ሚኒስቴር ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋራ ባካሄዱት ውይይት የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡ ድጋፉ በአሶሳ ለሚገነባው የዕምነበረድ ፓርክ እንዲሁም የአሶሳ የዕምነበረድ ማሰልጠኛን ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡በተጨማሪም ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የዕምነበረድ ሙያ ሰልጣኞች ወደ ጣልያን በመሄድ ስልጠና የሚያገኙ ይሆናል፡፡የተማረ የሰው ኃይላችንን ለማሳደግ የምንሰራው ስራም በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል፡፡
Read More

በክልሉ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሃብት ለማልማት በቅንጅት ይሠራል ተባለ።

አዲስ የተዋቀረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉት በርካታ የተፈጥሮ ሃብቶች ውስጥ ወርቅና የድንጋይ ከሠል ይጠቀሳሉ። በማዕድን ሚኒስቴር በሁለቱ ሚንስትር ዴኤታዎች የተመራ ልዑክም በክልሉ የ3 ቀናት የስራ ጉብኝት እና ከክልሉ ካቢኔ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል። ክልሉ በአዲስ በመዋቀሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገለገለ መኪና፣ 5 ኮምፒውተር፣ 1 ማባዣ ማሽን፣ 11 ተሽከርካሪ ወንበሮች እና ሌሎች የቢሮ ቁሳቁሶችን ድጋፍ […]
Read More

ከሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ

በየትኛውም ዘርፍ ወደፊት ለመጓዝ ሲታሰብ ሀገራዊ እድገታችንን የሚመጥን አቅርቦት ያስፈልጋል፡፡ በሲሚንቶ ምርት አቅርቦትን ለመጨመርና ለማሳደግ ከሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ከአመራሮቹ ጋር የሲሚንቶ ምርት መጨመር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ በመወያየት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በሲሚንቶ አመራቾች በኩል የተነሱ የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግሮችንም ለመፍታት ከተወሰኑ ወራት በኃላ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ለመተካት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
Read More
MoM