ከሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ

በየትኛውም ዘርፍ ወደፊት ለመጓዝ ሲታሰብ ሀገራዊ እድገታችንን የሚመጥን አቅርቦት ያስፈልጋል፡፡

በሲሚንቶ ምርት አቅርቦትን ለመጨመርና ለማሳደግ ከሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ከአመራሮቹ ጋር የሲሚንቶ ምርት መጨመር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ በመወያየት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በሲሚንቶ አመራቾች በኩል የተነሱ የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግሮችንም ለመፍታት ከተወሰኑ ወራት በኃላ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ለመተካት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Leave A Comment

MoM