በክልሉ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሃብት ለማልማት በቅንጅት ይሠራል ተባለ።

አዲስ የተዋቀረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉት በርካታ የተፈጥሮ ሃብቶች ውስጥ ወርቅና የድንጋይ ከሠል ይጠቀሳሉ።

በማዕድን ሚኒስቴር በሁለቱ ሚንስትር ዴኤታዎች የተመራ ልዑክም በክልሉ የ3 ቀናት የስራ ጉብኝት እና ከክልሉ ካቢኔ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

ክልሉ በአዲስ በመዋቀሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገለገለ መኪና፣ 5 ኮምፒውተር፣ 1 ማባዣ ማሽን፣ 11 ተሽከርካሪ ወንበሮች እና ሌሎች የቢሮ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል። የባህላዊ ወርቅ አምራቾች የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመፍታት በቅንጅት ይሠራል ተብሏል።

Leave A Comment

MoM