በወቅታዊ ሐገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሐገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ለውይይቱ “የድህረ ጦርነት መዛነፎችና እርምቶች” በሚል ርዕስ በድህረ ጦርነት ያሉ ተስፋዎችና ስጋቶች ከክልሎች ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ከብሔራዊ መግባባትና ከሀገር ግንባታ አንጻር የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡ ሰራተኞቻች ገንቢ የሆነ፣ ለሀገር ግንባታ ፋይዳው የጎላ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የማዕድንና ነዳጅ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በሠራተኞች የተነሱ ሐሳቦች ለሀገራዊ መግባባትና ሐገረ መንግስት ግንባታ መንግስት እጅግ ጠቃሚና እንደሆኑ እና ውይይቶችን በማድረግ እየሰራ እንደሆነ ገልፀው ለዚህም የህዝብ ድጋፍና ይቅር ባይነት ሊኖር እንደሚገባ መግባባት መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

Leave A Comment

MoM