ባለፉት አምስት ወራት ከማዕድን የወጪ ንግድ በተለይም ከወርቅ 241 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል። አሁን ካለንበት ሀገራዊ ሁኔታ በተለይም በማዕድን አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን ተቋቁመን የተመዘገው ውጤት አበረታች ነው። ያሉ ችግሮችን እየፈታንና እየሄድንበት ያለውን መንገድ አጠንክረን ከቀጠልን የማእድን ምርታችን የኢኮኖሚያችን ማገር መሆን እንደሚችል እየታየ ያለው ውጤት ማሳያ ነው ሲሉ የማዕድን ሚኒስቴር ሚንስትር ኢ/ር ታከለ ዑማ […]
አዲስ የተዋቀረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉት በርካታ የተፈጥሮ ሃብቶች ውስጥ ወርቅና የድንጋይ ከሠል ይጠቀሳሉ። በማዕድን ሚኒስቴር በሁለቱ ሚንስትር ዴኤታዎች የተመራ ልዑክም በክልሉ የ3 ቀናት የስራ ጉብኝት እና ከክልሉ ካቢኔ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል። ክልሉ በአዲስ በመዋቀሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገለገለ መኪና፣ 5 ኮምፒውተር፣ 1 ማባዣ ማሽን፣ 11 ተሽከርካሪ ወንበሮች እና ሌሎች የቢሮ ቁሳቁሶችን ድጋፍ […]
በየትኛውም ዘርፍ ወደፊት ለመጓዝ ሲታሰብ ሀገራዊ እድገታችንን የሚመጥን አቅርቦት ያስፈልጋል፡፡ በሲሚንቶ ምርት አቅርቦትን ለመጨመርና ለማሳደግ ከሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ከአመራሮቹ ጋር የሲሚንቶ ምርት መጨመር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ በመወያየት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በሲሚንቶ አመራቾች በኩል የተነሱ የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግሮችንም ለመፍታት ከተወሰኑ ወራት በኃላ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ለመተካት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
እድገትን መመኘት ብቻውን በቂ አይሆንም ፤ ያቀድነውን ለመፈፀም መትጋት ይጠበቃል። የማዕድን ሚኒስቴር የተሰጠው ኃላፊነትን ለመፈፀም ቅንጅትን ዋነኛ ማዕከሉ አድርጓል። በቅንጅት የማዕድን ወጪ ንግድን እናሳድጋለን ፤ከዚህ በሻገርም ከውጪ የሚገቡ የማዕድን ምርቶችን በሀገር ወስጥ ለማምረት ትክክለኛው መንገድ ላይ እንገኛለን። ይህ ሁሉ ሀሳብ ያለ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሰራተኞች የሚሳካ አይደለም፤ህልማችን ከሰራተኞቻችን ጋር በቅንጅት የምናሳካው ነው። ባለፉት ሁለት ቀናት የሚኒስቴር […]
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶክተር) አዲስ ባቋቋሙት ካቢኔ ክቡር ኢ/ር ታከለ ኡማ በንቲ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ የተሾሙ ሲሆን በማዕድን ዘርፍ የተጀመሩትን አመርቂ የስራ እንቅስቃሴዎች በበለጠ እንደሚያስቀጥሉ ሙሉ እምነት ተጥሎባቸዋል! ኢንጅነር ታከለ ዑማ ዘርፉን በመሩበት በአንድ ዓመት ውስጥ ከፍተኛው የውጭ ምንዛሬ መመዝገቡ ይታወቃል፡፡
በዘርፉ ሊከሰት የሚችለውን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመድፈን አገልግሎት አሰጣጡ ግልጽና ተጠያቂነትን ያማከለ የአሰራር ስርዓትን መዘርጋት ይገባል ተብሏል፡፡ ስልጠናው የአገር እድገት ማነቆ የሆነውን የሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ እና ለመቀነስ ይረዳል፡፡ በዘርፉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ምንጮችን በማሳየትና በቀጣይ ችግሩን ለመከላከል የሚጠቅሙ የማድረቂያ ስልቶችን በመንደፍ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ያስችላል፡፡ የሙስና እና ብልሹ አሰራር የአገር ሰላም የሚያናጋ […]
ከ6 የማዕድን ኩባንያዎች ጋር የምርት ፈቃድ ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስኪያጆች ተፈራርመዋል፡፡ ኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጣቸው የማዕድን ፍለጋውን አጠናቀውና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት ነው፡፡ ኩርሙክ ጎልድ ማይን ፣ኢትኖ ማይኒንግ እና ኦሮሚያ ማይኒንግ ኩባንያዎች የወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡ አሊ ሀሚል ካሐዲም የብሮሚን እና ክሎሪን ምርት ፈቃድ ወስዷል፡፡ […]
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባኪያሄደው ስብሰባ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የቀረቡለትን ሰባት የማአድን ምርት ፈቃዶች አጽድቋል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ስምምነቶቹ የሚኖራቸውን የአዋጭነት፣ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲሁም የኩባንያዎቹን ካፒታል በዝርዝር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበ ሲሆን ምክርቤቱም ይህን በመገንዘብ ስምምነቶቹን አጽድቆልናል፡፡ የሚፈረሙት ስምምነቶች ለሀገራችን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት በኩልም ይሁን ከፍተኛ የስራ እድል በመፍጠር በኩል ትልቅ ድርሻ የሚኖራቸው ይሆናል፡፡ከምንሰጣቸው ሰባት […]
የሚሰሩ ጠንካራ እጆች ሁሌም ድጋፍ ይገባቸዋል።የባህላዊ እና አነስተኛ ወርቅ አምራቾቻችን ለሀገራችን የማዕድን ክፍለ ኢኮኖሚ ዋልታ ሆነው ዘመናትን እያሻገሩን ይገኛሉ። እነሱን በተለያየ መንገድ መደገፍ ፣ከትከሻቸው ላይ ጫናዎችን ማቃለል ከእኛ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው። የክልሎቻችን ርእሰ መስተዳድሮች በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ ለሚያቀርቡት አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረውን የሮያሊቲ ክፍያን ሙሉ በሙሉ አንስተዋል። ይህ እርምጃ ለባህላዊ የማዕድን ምርት እንደሀገር […]
በማዕድን ዘርፍ ህግና ስርአትን ማስከበርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ስርአት ማስያዝ የቀጣዩ አመት እቅድ ስኬት ዋነኛው ግብአት የሚሆን ነው።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታና የቁጥጥር ስራዎችን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። ስምምነቱም ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባ ነው። በስምምነቱ መሰረትም በድንበር አካባቢዎች ህገወጥ የወርቅ ዝውውርና ለመከላከል ጠንካራ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ወርቅ ወይም ሌሎች ማዕድናት በሚወጣባቸው አካባቢዎች […]