የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረቡለትን ሰባት የማዕድን ምርት ፈቃዶች ተወያይቶ አጸደቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባኪያሄደው ስብሰባ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የቀረቡለትን ሰባት የማአድን ምርት ፈቃዶች አጽድቋል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ስምምነቶቹ የሚኖራቸውን የአዋጭነት፣ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲሁም የኩባንያዎቹን ካፒታል በዝርዝር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበ ሲሆን ምክርቤቱም ይህን በመገንዘብ ስምምነቶቹን አጽድቆልናል፡፡

የሚፈረሙት ስምምነቶች ለሀገራችን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት በኩልም ይሁን ከፍተኛ የስራ እድል በመፍጠር በኩል ትልቅ ድርሻ የሚኖራቸው ይሆናል፡፡ከምንሰጣቸው ሰባት የምርት ፈቃዶች መሀልም አራቱ የወርቅ ምርት ሁለቱ የእምነበረድ ምርት አንዱ ደግሞ ብሮሚንና ክሎሪን ምርት ላይ የሚሰማሩ ናቸው።

Leave A Comment

MoM