የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ሠራተኞች የ3 ወር ስራ ግምገማ እና የቀጣይ 3ወር እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

እድገትን መመኘት ብቻውን በቂ አይሆንም ፤ ያቀድነውን ለመፈፀም መትጋት ይጠበቃል። የማዕድን ሚኒስቴር የተሰጠው ኃላፊነትን ለመፈፀም ቅንጅትን ዋነኛ ማዕከሉ አድርጓል።

በቅንጅት የማዕድን ወጪ ንግድን እናሳድጋለን ፤ከዚህ በሻገርም ከውጪ የሚገቡ የማዕድን ምርቶችን በሀገር ወስጥ ለማምረት ትክክለኛው መንገድ ላይ እንገኛለን።

ይህ ሁሉ ሀሳብ ያለ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሰራተኞች የሚሳካ አይደለም፤ህልማችን ከሰራተኞቻችን ጋር በቅንጅት የምናሳካው ነው።

ባለፉት ሁለት ቀናት የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችንን የ3 ወር ስራ የገመገምን ፣ የቀጣይ 3ወር እቅድ ላይም የተግባባን ሲሆን መገንባት ስላለብን ተቋማዊ የስራ ባህልም በስልጠና የታጀበ ውይይት አድርገናል።

ቆይታችን ከተለመደው የስራ ባህል ተላቀን አዲስ የስራ ባህል ለመፍጠር የሚያግዘን ነው።

ለሀገራችን መልካም ሥራ ለመሥራት የሁላችንም ለውጥ ትልቅ ቦታ አለው።

Leave A Comment

MoM