በዘርፉ ሊያጋጥም የሚችለውን ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመድፈን የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ

በዘርፉ ሊከሰት የሚችለውን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመድፈን አገልግሎት አሰጣጡ ግልጽና ተጠያቂነትን ያማከለ የአሰራር ስርዓትን መዘርጋት ይገባል ተብሏል፡፡

ስልጠናው የአገር እድገት ማነቆ የሆነውን የሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ እና ለመቀነስ ይረዳል፡፡ በዘርፉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ምንጮችን በማሳየትና በቀጣይ ችግሩን ለመከላከል የሚጠቅሙ የማድረቂያ ስልቶችን በመንደፍ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ያስችላል፡፡

የሙስና እና ብልሹ አሰራር የአገር ሰላም የሚያናጋ እና የህግ የበላይነትን የሚያጠፋ በመሆኑ የችግሩን አደጋነት ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል፡፡ በተቋማችንም ሙስናና ብልሹ አሰራርን አጥብቆ በመጥላትና በመፀየፍ ህዝብና መንግስትን ማገልገል ይጠበቃል፡፡

በዘርፋችን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኑ የዘርፋን አገልግሎቶች በሚገባ በመለየትና ችግሮቹ እንዳይከሰቱ ለመድፈን የሚያስችሉ ስልቶችን እና አሰራሮችን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡

በዕለቱ በዘርፉ ተጋላጭ የሆኑ የስራ ክፍሎች የስራ ክፍላቸውን ተጋላጭነትንና የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት እየሰሩት ያለውን እቅድ አቅርበዋል፡፡

Leave A Comment

MoM