በማዕድን ዘርፍ ህግና ስርዓትን ለማስከበርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ስርዓት ለማስያዝ ይሰራል

በማዕድን ዘርፍ ህግና ስርአትን ማስከበርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ስርአት ማስያዝ የቀጣዩ አመት እቅድ ስኬት ዋነኛው ግብአት የሚሆን ነው።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታና የቁጥጥር ስራዎችን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። ስምምነቱም ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባ ነው።

በስምምነቱ መሰረትም በድንበር አካባቢዎች ህገወጥ የወርቅ ዝውውርና ለመከላከል ጠንካራ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ወርቅ ወይም ሌሎች ማዕድናት በሚወጣባቸው አካባቢዎች ባሉ አዘዋዋሪዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻ የሚደረግ ይሆናል፡፡በተጨማሪም እነዚህ የጸጥታ ስራዎች በተደራጀና ወጥ በሆነ መልኩ መከናወን እንዲችሉ “የማአድን ፖሊስ ዲፓርትመንት” ይደራጃል። ውይይቱ ወደ ተግባር እንዲቀየርና በሰነድ እንዲደገፍ ከፍተኛ ሚና የነበራቸውን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና ኢንጅነር ታከለ ዑማ ስምምነቱን ተፋራርመዋል፡፡

Leave A Comment

MoM