የከፍተኛ ማዕድን ምርት ፈቃድ ተሰጠ

ከ6 የማዕድን ኩባንያዎች ጋር የምርት ፈቃድ ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስኪያጆች ተፈራርመዋል፡፡

ኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጣቸው የማዕድን ፍለጋውን አጠናቀውና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት ነው፡፡ ኩርሙክ ጎልድ ማይን ፣ኢትኖ ማይኒንግ እና ኦሮሚያ ማይኒንግ ኩባንያዎች የወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡ አሊ ሀሚል ካሐዲም የብሮሚን እና ክሎሪን ምርት ፈቃድ ወስዷል፡፡ ኪሪፕቶ ማይኒንግ ኤንድ ኬሚካልስ እና ቡሁሚ ማይኒንግ ኩባንያዎች ደግሞ የእምነበረድ ምርት ፈቃድ ወስደዋል፡፡

ኩባንያዎቹ ከ4.7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገቡ ሲሆን ከ1300 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ቋሚ የስራ እድል ይፈጥራሉ፡፡

Leave A Comment

MoM