ለክልሎች ሲከፈል የነበረው የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተነሳ

የሚሰሩ ጠንካራ እጆች ሁሌም ድጋፍ ይገባቸዋል።የባህላዊ እና አነስተኛ ወርቅ አምራቾቻችን ለሀገራችን የማዕድን ክፍለ ኢኮኖሚ ዋልታ ሆነው ዘመናትን እያሻገሩን ይገኛሉ።

እነሱን በተለያየ መንገድ መደገፍ ፣ከትከሻቸው ላይ ጫናዎችን ማቃለል ከእኛ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው።

የክልሎቻችን ርእሰ መስተዳድሮች በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ ለሚያቀርቡት አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረውን የሮያሊቲ ክፍያን ሙሉ በሙሉ አንስተዋል።

ይህ እርምጃ ለባህላዊ የማዕድን ምርት እንደሀገር የሰጠነው ትኩረት ማሳያ ነው።

በሌላ መልኩ ደግሞ በህገወጥ መንገድ የሃገር ሀብት ላይ አሻጥር ለሚሠሩት ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

Leave A Comment

MoM