የኖርዌዩ አኮቦ ሚኔራልስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሰገሌ የወርቅ ማዕድን ቦታ ወርቅ እና አብረው የሚገኙ ማዕድናትን ለማውጣት የሚያስችለውን ፈቃድ አግኝቶ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ የአኮቦ ሚኔራልስ ኩባንያ ኃላፊ ጆርገን ኤቭጄን÷ኩባንያቸው በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ ሲወስን እንዴት ግጭት በተቀሰቀሰበት የጦር ቀጠና ትሄዳላችሁ የሚሉ ጥያቄዎች ከሌሎች አቻ ኩባንያዎች ሲቀርብላቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ከኩባንያዎቹ የማስጠንቀቂያ አስተያየቶች በተጨማሪ አዲስ አበባ በአሸባሪው እጅ ወድቃለች […]
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት (2013) ከማዕድን ምርቶቻችን 681 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝተናል። ይህም ባለፋት ዓመታት ከተገኘው የውጭ ምንዛሪ ትልቁ በመሆን ተመዝግቧል። በቀጣይ ዓመትም ከዘርፉ ከዚህ የተሻለ ለማግኘት እቅድ አስቀምጠን ወደ ተግባር ገብተናል። ያሰብነውን ሳናሳካ እረፍት የለንም! ያሰብነውን እንደምናሳካና የማአድን ሀብታችንም የኢኮኖሚያችን ዋልታ እንደሚሆን እየሄድንበት ያለው መንገድ የሚታይ ምስክር ነው።
ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት በICL ((Israel Chemical Limited) በተባለ የፖታሽ ማዕድን አውጪ ኩባንያ የተመሰረትባትን የ300 ሚሊዮን ዶላር ክስ በትናንትናው ዕለት በአሸናፊነት ተወጥታለች። ክሱ የቀረበበትና ይግባኝ የማይባልበትን ፍርድ የሰጠው በሄግ ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት (Permanent Court of Arbitration) ነው በክርክሩ ሂደት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳታፊ ለነበራችሁ ሁሉ፤ በተለይም የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስቴርና […]
በተያዘው አመትም በታሪካችን ከፍተኛውን ገቢ ከማአድን ዘርፍ አግኝተናል። በ11 ወር ብቻ ከ668 ሚሊዮን ዶላር በላይ አግኝተናል። በቀጣይ አመትም ከዘርፉ 1.5 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት እቅድ አስቀምጠን ከክልሎች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል። እቅዳችን እንዲሳካም በዘርፉ እየታዩ ያሉ ችግሮችን ማስተካከል ከኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው።በማዕድን ማውጫ አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በተመለከተ በሰላም ሚኒስቴር በኩል መፍትሄ የሚያገኝ መሆኑን መግባባት ላይ […]
የድንጋይ ከሰልን በሀገር ውስጥ ለማምረት ላሰብነው ሀሳብ ሁለተኛውን እርምጃ ተራምደናል። በዛሬው እለትም ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን በአሶሳ ሁለተኛውን የከሰል ድንጋይ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ አስጀምረናል ። ፋብሪካውን NOC የሚያስገነባውና በ11 ወራት የሚጠናቀቅ ይሆናል። በቀጣይ ቀናትም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ተጨማሪ የድንጋይ ከሰል ማምረቻዎችን ግንባታ እናስጀምራለን። ፋብሪካዎቹ ማምረት ሲጀምሩ ሀገራዊ የማምረት አቅማችን […]
ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር የ10 ወራትን አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በገቡት የስራ ውል መሰረት ወደ ስራ ያልገቡ የምርትና የምርመራ ፈቃዶችን ውላቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት አላቂ የሆነው የማዕድን […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ለማካሄድ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ። ስምምነቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚያዚያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል በተካሄደው መርሃግብር ላይ ተፈራርመዋል። የመግባቢያ ሰነዱ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ […]
የፌዴራል የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በማዕድን ዘርፍ የሚስተዋለውን ተግዳሮቶችን “national study on the prevention of corrupt practices in the mining sector” በሚል ባስጠናው ጥናት ላይ የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ በጥናቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ‹‹ማዕድን የማይተካ የተፈጥሮ ሃብት በመሆኑ ዘርፉ […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በሚኔራል፣ በፔትሮሊየምና ፔትሮኬሚካል ኢንጂነሪግ የሁለተኛ ዲግሪ የስረዓተ ትምህርት ቀረጻ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ የትምህርት ዘርፎቹ በዘርፍ ያለውን የባለሙያ እጥረት የሚፈታ ነው፡፡ የትምህርት አሰጣጡ ከንድፈ-ሃሳብ በዘለለ በተግባር የሚሰጥ ነው፡፡ በቀጣዮቹ 10 አመታት ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ 675 ተማሪዎችን ለማስተማር እቅድ ተይዟል፡፡ በዘንድሮው አመትም 50 ተማሪዎችን ለመቀበል የቅድመ […]
ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለመጠቀም የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ በወረቀት የሚያዙ መረጃዎች የመበላሸት፣ የመቀደድ፣ የመጥፋት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ፈልጎ ለማግኘት አዳጋች ናቸው፡፡ ስልጠና የወረቀት ፋይል የመረጃ አያያዝ ስርዓት የሚቀይር ነው፡፡ በሶፍትም ሆነ በሃርድ ኮፒ የሚመጡ መረጃዎችን ማስገባት የሚያስችል አቅም የሚፈጥር ነው፡፡ ስልጠናው ሲጠናቀቅ ሙሉ በሙሉ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመዝገብ […]