በማዕድን ዘርፍ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለማስቀረትና ለመከላከል የሁሉም ሚና ከፍተኛ ነው ተባለ!

የፌዴራል የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በማዕድን ዘርፍ የሚስተዋለውን ተግዳሮቶችን “national study on the prevention of corrupt practices in the mining sector” በሚል ባስጠናው ጥናት ላይ የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
በጥናቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ‹‹ማዕድን የማይተካ የተፈጥሮ ሃብት በመሆኑ ዘርፉ ለሀገሪቱ ከፍተኛ ውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ለአገር ውስጥ ኢንዱስት ግብዓት በመሆንና ከውጭ የሚገቡትን ማዕድናት በአገር ውስጥ ማዕድናት በመተካት ከፈተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑንና በአግባቡ ከተመራ ለሃገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም መንግስትም ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው መሆኑን ጠቅሰው በ2004 ዓ.ም ከዘርፉ የተገኘውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በዚህ ዓመት ለመድገም አየተሰራ ባለው ስራ ባለፉት ስምንት ወራት የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን ጠቅሰው ዘርፉ ሊጋጥሙት የሚቸሉ ተግዳሮቶችን ከወዲሁ አውቆ ለመከላከል እንዲህ አይነት ጥናት መደረጉ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ አክሊሉ ሙሉጌታ የፌዴራል ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስነ-ምግባር መከታተያና የሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ‹‹በዘርፉ የተካሄደው ጥናት ዋና ዓላማው የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራርን መከላከል አንዱ ዓላማ በመሆኑ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የማዕድን ዘርፍ ለሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ በመሆኑ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማሳየት ነው፡፡››ብለዋል፡፡
አቶ ጌዲዮን ገሙላ የጥናቱ ዋና ተመራማሪ የጥናቱን መነሻ፣ ግኝቶች፣ የመፍትሔ ሃሳቦችና ቀጣይ የሰራ አቅጣጫዎችን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡

Leave A Comment

MoM