የማዕድን ዘርፉን ክፍተት በሚሞሉ የስርዓተ ትምህርት ቀረጻ ላይ የምክክር መድረክ እየተደረገ ነው

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በሚኔራል፣ በፔትሮሊየምና ፔትሮኬሚካል ኢንጂነሪግ የሁለተኛ ዲግሪ የስረዓተ ትምህርት ቀረጻ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
የትምህርት ዘርፎቹ በዘርፍ ያለውን የባለሙያ እጥረት የሚፈታ ነው፡፡ የትምህርት አሰጣጡ ከንድፈ-ሃሳብ በዘለለ በተግባር የሚሰጥ ነው፡፡
በቀጣዮቹ 10 አመታት ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ 675 ተማሪዎችን ለማስተማር እቅድ ተይዟል፡፡ በዘንድሮው አመትም 50 ተማሪዎችን ለመቀበል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን የማዕድን ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ተናግረዋል፡፡

Leave A Comment

MoM