ኢትዮጵያ ከማዕድን ሀብቷ እያገኘች ያለችው ገቢ በከፍተኛ መጠን ጭማሪ እያሳየ ይገኛል

በተያዘው አመትም በታሪካችን ከፍተኛውን ገቢ ከማአድን ዘርፍ አግኝተናል።  በ11 ወር ብቻ ከ668 ሚሊዮን ዶላር በላይ አግኝተናል። በቀጣይ አመትም ከዘርፉ 1.5 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት እቅድ አስቀምጠን ከክልሎች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል።

እቅዳችን እንዲሳካም በዘርፉ እየታዩ ያሉ ችግሮችን ማስተካከል ከኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው።በማዕድን ማውጫ አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በተመለከተ በሰላም ሚኒስቴር በኩል መፍትሄ የሚያገኝ መሆኑን መግባባት ላይ ደርሰናል። ከክልሎች ጋር በነበረን ውይይት ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ዲኤታ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባውን ላመሰግን እወዳለው።

በቀጣይ በተባበረ መልኩ ሰርተን እቅዳችንን የምናሳካ ይሆናል።

Leave A Comment

MoM