የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከተቋሙና ከተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር የዘርፉን የሰባት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቧል። ከባለፈው በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በተሻለ ሁኔታ ከዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። በተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም ተግባራት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ገልጸዋል። መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት የሠጠው በመሆኑ አመራሩና ሠራተኛው በጋራ ተናቦ […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሲሚንቶ ፋብሪካ ሃላፊዎችና ከድንጋይ ከሰል አምራቾች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰልን በሃይል ምንጭንት ይጠቀማሉ፡፡ የድንጋይ ከሰልን ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት የሚጠቀሙት ፋብሪካዎች በአሁኑ ጊዜ በሐገር ውስጥ የሚመረተውን የድንጋይ ከሰል ከ40 እስከ 60 ፐርሰንት መጠቀም የጀመሩ ሲሆን በሂደት ሙሉ በሙሉ የአገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ለመጠቀም የሚያስችል […]
ጉብኝት ያዘጋጀው ‘Allied Gold Cop’ የተባለ የማዕድን ልማት ኩባንያ ሲሆን ኩባንያው በቤንሻንጉል-ጉምዝ፣ አሶሳ ዞን፣ ኩርሙክ ወረዳ ዲሽ እና አሻሽሬ በተባሉ ቦታዎች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሊለሙ የሚችሉ ሁለት (2) የወርቅ ክምችት ምርመራ በማድረግ በቅርቡ ወደ ልማት ለመሸጋገር የምርት ፈቃድ ለመውሰድ የተዘጋጀ ኩባንያ ነው፡፡ ሰባት አባላትን የያዘው የልዑካን ቡድኑ የተውጣጣው ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር፣ ከክልሉ ማዕድን ልማት ኤጀንሲ፣ […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት አስመረቀ።የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እና የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፕሮጀክቱን መርቀው ከፍተውታል። የተመረቀው ፕሮጀክት በድሬዳዋ ከተማ ለ700 የገንደ ሪጌ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ 1.8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ፓዮኔር ከተባለ የሲሚንቶ ኩባንያ ነው።የማዕድን ኩባንያዎች ማዕድንን […]
በማዕድንና ነዳጅ ዘርፎች የማዕድን የምርት አቅርቦት በማሳደግ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እና የ2013 ዓ.ም የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት የተደረገው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ነው ፡፡ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሚኒስቴር መስሪያ […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እና የስራ ሃላፊዎች የጌጣጌጥ ማዕድን ላኪዎችን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል::
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል። ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዘሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ፤ ወርቅ፣ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፓየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡ ወርቅን በተመለከተ በባህላዊ መንገድ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 2ሺህ 241 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል፡፡ በእቅድነት ተይዞ የነበረው 251 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ […]
ኢ/ር ታከለ ኡማ በሲዳማ ክልል የገናሌ ወንዝ ገባር በሆነው በሎጌታ ወንዝ ዳር ወርቅ ለማውጣት በሂደት ላይ የሚገኘውን የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ተመልክተዋል። የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ካምፓኒ ከሁለት ወር በኋሏ ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገ ነው። ካምፓኒው በአካባቢው ተወላጆች እና ነዋሪዎች ባለቤትነት የሚመራ እና የሚበረታታ መሆኑንም ኢ/ር ታከለ ተናግረዋል። አካባቢው ከፍተኛ የመንገድና የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት በመሆኑ […]
ኢ/ር ታከለ ከአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጋር በመሆን የፖታሽ፣ ጨውና ብሮሚን ምርቶች ላይ እየተከናወኑ ያሉ የማአድን ልማቶችን ተመልክተዋል። ኢ/ር ታከለ አፍዴራ አካባቢ “ታናራሙ ኬሚካልስ” በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገባ የሚገኘው የብሮሚን ፋብሪካ የጎበኙ ሲሆን ፋብሪካው በ57 ሚሊየን ዶላር ወጪ እየተገነባ የሚገኝ ነው። ፋብሪካው “ሀይድሮጅን ብሮማይድ አሲድ” አዘጋጅቶ ለውጪ ገበያ የሚያቀርብ ይሆናል። ፋብሪካው በቅርብ […]
በጉብኝቱ ላይም የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።