ኢ/ር ታከለ ኡማ በሲዳማ ክልል በሎጌታ ወንዝ ዳር ወርቅ ለማውጣት በሂደት ላይ የሚገኘውን የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ተመልክተዋል

ኢ/ር ታከለ ኡማ በሲዳማ ክልል የገናሌ ወንዝ ገባር በሆነው በሎጌታ ወንዝ ዳር ወርቅ ለማውጣት በሂደት ላይ የሚገኘውን የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ተመልክተዋል።
የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ካምፓኒ ከሁለት ወር በኋሏ ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገ ነው።
ካምፓኒው በአካባቢው ተወላጆች እና ነዋሪዎች ባለቤትነት የሚመራ እና የሚበረታታ መሆኑንም ኢ/ር ታከለ ተናግረዋል።
አካባቢው ከፍተኛ የመንገድና የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት በመሆኑ ችግሩን መፍታት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ጋርም ተወያይተዋል።
ችግሮችን ለመፍታት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

Leave A Comment

MoM