ባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶለር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኘ

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።
ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዘሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ፤ ወርቅ፣ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፓየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡
ወርቅን በተመለከተ በባህላዊ መንገድ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 2ሺህ 241 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል፡፡
በእቅድነት ተይዞ የነበረው 251 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ለማቅረብ ነበር፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል የተደረገው የወርቅ ማሻሻያ ዋጋ የወርቅ አቅራቢዎችን በመሳቡ ምክንያት ከታቀደው በ298ነጥብ9 በላይ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል።
በተጨማሪም ባለፉት ሶስት ወራት የተቋሙ የ10 አመት እቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ለሚመለከታቸው አካላትም ተልኳል።
የማአድንና ነዳጅ ዘርፉ የፖሊሲ ማሻሻያም ተደርጎበታል ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።
በሀገሪቷ የሌለውን የወርቅ ቤተ ሙከራ ለማቋቋም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከተለያዩ ተቋማት ጋር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በማአድንም ይሁን በነዳጅ ዘርፍ ላይ ላይ የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን የህግና ተግባራዊ ማሻሻያዎች እየተሰሩ መሆኑን ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።
ቀጣይ ጊዜያትም የተጀመሩ የሰነድ ስራዎች የሚጠናቀቁበትና ተቋማዊ ግንባታው ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ይሆናል ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።

Leave A Comment

MoM