የድንጋይ ከሰልን ለማቅረብ በቅንጅት መስራት ይገባል ተባለ

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሲሚንቶ ፋብሪካ ሃላፊዎችና ከድንጋይ ከሰል አምራቾች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡
ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰልን በሃይል ምንጭንት ይጠቀማሉ፡፡ የድንጋይ ከሰልን ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት የሚጠቀሙት ፋብሪካዎች በአሁኑ ጊዜ በሐገር ውስጥ የሚመረተውን የድንጋይ ከሰል ከ40 እስከ 60 ፐርሰንት መጠቀም የጀመሩ ሲሆን በሂደት ሙሉ በሙሉ የአገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ለመጠቀም የሚያስችል አቅም ከወዲሁ ሊፈጠር እንደሚገባ በውይይቱ መግባባት ላይ ተደርሰል፡፡
ከተወያዮች ጋር በተደረገ ውይይት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እና የድንጋይ ከሰል አምራቾች የትራንስፖርት እጥረትና የዋጋ መናር፣ የገበያ ትስስር አለመኖር፣ የድንጋይ ከሰል ጥራት ችግር፣ የህገ-ወጥ ደላሎች፣ የመንገድ ችግር፣ የላብራቶሪ ወጥነት የሌለው መሆኑ፣ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮችና አላግባብ የተለያዩ ክፍያዎች መጠየቅ ከተነሱት ዋና ዋናዎቹ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ዮሐንስ ድንቃየሁ ከሲሚንቶ ፋብሪካ ሃላፈዎች፣ ከድንጋይ ከሰል አምራቾች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ችግር በመለየት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት በአጭር እና በረጅም ጊዜ ሊፈቱ ስለሚገባቸው ችግሮች የመፍትሄ ሃሳቦችን በማመላከት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
በቀጣይ አማራቾችና ተጠቃሚዎች በቅንጅት የሚሰሩበት ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡

Leave A Comment

MoM