የሴቶች ቀን ተከበረ

በሐገራችን ለ45ኛ በዓለም ደግሞ ለ110ኛ ጊዜ የተከበረውን የሴቶች ቀን ማርች 8 አከበረ፡፡
የዘንድሮው የዓለም የሴቶች ቀን እየተከበረ ያለው ‹‹የሴቶችን መብት የሚያስከብር ማህበረሰብ እንገንባ›› የሚል መሪ ነው፡፡
የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ በመክፈቻ ንግግራቸው በሴቶች ላይ የሚደርሱ ዘርፈ ብዙ ጥቃቶችን ለማስቆም በተለይም ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ በማለት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ትግላቸውን በመጀመር ዛሬ ለደረስንበት ትግል ፈር ቀዳጅ ነው ብለዋል፡፡
የሴቶችን መብቶች ለማስከበር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ቢደረጉም አጥጋቢ አለመሆኑንና ሴቶች የራሳቸውን መብት ለማስከበር በጋራ መቆም ይገባል አክለዋል፡፡
ከሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ በዓሉ አጀማመር ገለጻ የተሰጠ ሲሆን የማነቃቂያ ንግግሮችም በወ/ሮ መቅደስ ገ/ወልድ ከአሻጋሪ ኮንሱልታንት ተደርጓል፡፡

Leave A Comment

MoM