በማህበረሰብ ልማት ፈንድ የተሰራ ፕሮጀክት ተመረቀ::

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት አስመረቀ።የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እና የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፕሮጀክቱን መርቀው ከፍተውታል።

የተመረቀው ፕሮጀክት በድሬዳዋ ከተማ ለ700 የገንደ ሪጌ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ 1.8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ፓዮኔር ከተባለ የሲሚንቶ ኩባንያ ነው።የማዕድን ኩባንያዎች ማዕድንን የሚያለሙበት አካባቢ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን አንዲወጡ የሚያስችል የማህበራዊ ልማት ክፍያ ነው።

በቀጣይም በ4 ሚሊዮን ብር የመጠጥ ውሃ እና ሌሎች አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች እንዲያገኙ እየተሰራ ነው፡፡ፓዮኔር ኩባንያ ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድልም ፈጥሯል፡፡

ከምረቃ ስነ-ስርዓት በኋላም የስራ ሃላፊዎቹ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘውን የናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል

Leave A Comment

MoM