ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘርፉን የሰባት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከተቋሙና ከተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር የዘርፉን የሰባት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቧል።
ከባለፈው በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በተሻለ ሁኔታ ከዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል።
በተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም ተግባራት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ገልጸዋል። መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት የሠጠው በመሆኑ አመራሩና ሠራተኛው በጋራ ተናቦ በመስራት የተጣለብንን ሃገራዊ ተልዕኮ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የቀጣይ 5 ወራት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችም ቀርበዋል።
በቀጣይ 10 ዓመት ከዘርፉ ከ17 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘትም ታቅዷል።
የሲቪል ሠርቪስ ፍኖተ ካርታም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በህዝብ በሚመረጥ መንግሥት የሚነድፋቸውን የልማት ዕቅዶች ማሳካት የሚችል፣ የህዝብ አገልጋይነትን መንፈስ የተላበሰና ነጻ፣ገለልተኛና ብቃት ያለው የመንግስት አገልግሎት ስርዓት መገንባት የፍኖተ ካርታው ዋናው ዓላማ ነው።

Leave A Comment

MoM