የፌዴራል የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በማዕድን ዘርፍ የሚስተዋለውን ተግዳሮቶችን “national study on the prevention of corrupt practices in the mining sector” በሚል ባስጠናው ጥናት ላይ የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ በጥናቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ‹‹ማዕድን የማይተካ የተፈጥሮ ሃብት በመሆኑ ዘርፉ […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በሚኔራል፣ በፔትሮሊየምና ፔትሮኬሚካል ኢንጂነሪግ የሁለተኛ ዲግሪ የስረዓተ ትምህርት ቀረጻ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ የትምህርት ዘርፎቹ በዘርፍ ያለውን የባለሙያ እጥረት የሚፈታ ነው፡፡ የትምህርት አሰጣጡ ከንድፈ-ሃሳብ በዘለለ በተግባር የሚሰጥ ነው፡፡ በቀጣዮቹ 10 አመታት ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ 675 ተማሪዎችን ለማስተማር እቅድ ተይዟል፡፡ በዘንድሮው አመትም 50 ተማሪዎችን ለመቀበል የቅድመ […]
ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለመጠቀም የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ በወረቀት የሚያዙ መረጃዎች የመበላሸት፣ የመቀደድ፣ የመጥፋት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ፈልጎ ለማግኘት አዳጋች ናቸው፡፡ ስልጠና የወረቀት ፋይል የመረጃ አያያዝ ስርዓት የሚቀይር ነው፡፡ በሶፍትም ሆነ በሃርድ ኮፒ የሚመጡ መረጃዎችን ማስገባት የሚያስችል አቅም የሚፈጥር ነው፡፡ ስልጠናው ሲጠናቀቅ ሙሉ በሙሉ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመዝገብ […]
በሐገራችን ለ45ኛ በዓለም ደግሞ ለ110ኛ ጊዜ የተከበረውን የሴቶች ቀን ማርች 8 አከበረ፡፡ የዘንድሮው የዓለም የሴቶች ቀን እየተከበረ ያለው ‹‹የሴቶችን መብት የሚያስከብር ማህበረሰብ እንገንባ›› የሚል መሪ ነው፡፡ የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ በመክፈቻ ንግግራቸው በሴቶች ላይ የሚደርሱ ዘርፈ ብዙ ጥቃቶችን ለማስቆም በተለይም ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ በማለት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ትግላቸውን በመጀመር ዛሬ ለደረስንበት […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከተቋሙና ከተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር የዘርፉን የሰባት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቧል። ከባለፈው በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በተሻለ ሁኔታ ከዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። በተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም ተግባራት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ገልጸዋል። መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት የሠጠው በመሆኑ አመራሩና ሠራተኛው በጋራ ተናቦ […]
ከኢትዮጵያዊያንም አልፎ ለመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነው ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!! አድዋ የብሔራዊ ኩራታችን ምንጭ!
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሲሚንቶ ፋብሪካ ሃላፊዎችና ከድንጋይ ከሰል አምራቾች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰልን በሃይል ምንጭንት ይጠቀማሉ፡፡ የድንጋይ ከሰልን ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት የሚጠቀሙት ፋብሪካዎች በአሁኑ ጊዜ በሐገር ውስጥ የሚመረተውን የድንጋይ ከሰል ከ40 እስከ 60 ፐርሰንት መጠቀም የጀመሩ ሲሆን በሂደት ሙሉ በሙሉ የአገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ለመጠቀም የሚያስችል […]
ጉብኝት ያዘጋጀው ‘Allied Gold Cop’ የተባለ የማዕድን ልማት ኩባንያ ሲሆን ኩባንያው በቤንሻንጉል-ጉምዝ፣ አሶሳ ዞን፣ ኩርሙክ ወረዳ ዲሽ እና አሻሽሬ በተባሉ ቦታዎች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሊለሙ የሚችሉ ሁለት (2) የወርቅ ክምችት ምርመራ በማድረግ በቅርቡ ወደ ልማት ለመሸጋገር የምርት ፈቃድ ለመውሰድ የተዘጋጀ ኩባንያ ነው፡፡ ሰባት አባላትን የያዘው የልዑካን ቡድኑ የተውጣጣው ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር፣ ከክልሉ ማዕድን ልማት ኤጀንሲ፣ […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት አስመረቀ።የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እና የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፕሮጀክቱን መርቀው ከፍተውታል። የተመረቀው ፕሮጀክት በድሬዳዋ ከተማ ለ700 የገንደ ሪጌ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ 1.8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ፓዮኔር ከተባለ የሲሚንቶ ኩባንያ ነው።የማዕድን ኩባንያዎች ማዕድንን […]