ኢ/ር ታከለ ኡማ በማአድንና ነዳጅ ዘርፍ እምቅ ሀብት የተለዩ ቦታዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን በተመለከተ ለረጅም ጊዜያት የተጠኑ ጥናቶችን በጋራ በማደራጀት ለምርት ዝግጁ የሆኑ ቦታዎች መለየታቸውም ተገልጿል።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል። ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዘሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ፤ ወርቅ፣ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፓየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡ ወርቅን በተመለከተ በባህላዊ መንገድ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 2ሺህ 241 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል፡፡ በእቅድነት ተይዞ የነበረው 251 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ […]
ኢ/ር ታከለ ኡማ በቤኔሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኙ የማዕድን ማውጫ ቦታዎችን ከክልሉ ርዕሰመስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን ተመልክተዋል። አሻሽሬ አካባቢ ወርቅ በማውጣት ሂደት ላይ የሚገኘውን “አስኮም ማይኒንግ” ከተመለከቷቸው ቦታዎች አንዱ ነው። ካምፓኒው በአካባቢው ወርቅ እና የከበሩ ማዕድናትን በማፈላለግ ሂደት ላይ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ወደ ምርት ለመግባት የሚያስችለውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል። ሚንስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ […]
Biyya Warqee fi Bunaa, Biyya dhadhaa fi dammaa wallagga oolle har’a. Dargaggoon baayy’een oomisha warqee aadaadhaan oomishan dinagdeen of danda’uuf xaaraa jiran jajjaabeessuuf. Dargaggoo baayy’eetu hojii jalqabaniii bu’aa argachuu ifaajaa jiru. Nutis meeshaa oomisha warqee adaaf ta’u deegaruuf ni hojjenna. Rakkoo idoo gurgurtaa warqee kan tures baankiiin daldalaa Itoophiyaa wiirtuu Gimbitti akka irraa bituuf damee […]
በጉብኝቱ ላይም የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
በአራት ወር ውስጥ ከ3600 ኪ.ግ በላይ ወርቅ ለውጪ ገበያ ቀርቧል። ኢ/ር ታከለ ኡማ በማዕድን ዘርፍ አፈፃፀምና ቀጣይ እቅዶች ዙሪያ ከክልል የማዕድን ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንደተናገሩት መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሠጥቶ እየሰራ ሲሆን ባለፉት አራት ወራት 3602.8 ኪሎግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 265.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ከጌጣጌጥ ማዕድናት ደግሞ 3.215 […]
የኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ እና 61ኛ የቦርድ ስብሰባውን ከባለድርሻ አካላት ጋር በሃያት ሬጀንሲ አካሄዷል። በቦርድ ስብሰባው 5ኛ እና 6ኛ የኢኒሼቲቩ ሪፖርት ያለበት ደረጃ የቀረበ ሲሆን በዘርፉ የባለድርሻ አካላት አስተዋፆን ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል። መንግስት ፖለቲካዊ አመራር እና ድጋፍ መስጠት፣ ህግን ማውጣትና መከታተል ይኖርበታል ።
የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ፈቃዳቸው በተሰረዘው ተቋማትና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የማድን ፈቃድ አውጥተው በተገቢው መልኩ ጥቅም ላይ ያላዋሉ ተቋማት ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እርምጃ መውሰዱንም ኢ/ር ታከለ ገልጸዋል፡፡ በተገቢው ወቅት የተሰጣቸውን ፈቃድ ያለማደስ፣ በውል የገቡትን ግዴታ ባለማክበር፣ከአቅም በታች በማምረት እንዲሁም የሮያሊቲ ክፍያ ባለመፈጸም ምክንያት የተሰጣቸው ፈቃድ እንዲሰረዝ ምክንያት ሆኗል፡፡ ፈቃዳቸው ከተቋረጠው […]