ከማዕድን ዘርፍ ባለፉት አራት ወራት 269.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

በአራት ወር ውስጥ ከ3600 ኪ.ግ በላይ ወርቅ ለውጪ ገበያ ቀርቧል።
ኢ/ር ታከለ ኡማ በማዕድን ዘርፍ አፈፃፀምና ቀጣይ እቅዶች ዙሪያ ከክልል የማዕድን ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንደተናገሩት መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሠጥቶ እየሰራ ሲሆን ባለፉት አራት ወራት 3602.8 ኪሎግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 265.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
ከጌጣጌጥ ማዕድናት ደግሞ 3.215 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተገኝቷል።
በእቅድነት የተያዘው የወርቅ ምርት የተከለሰ ሲሆን በተሻለ መንገድ ኢኮኖሚውን መደገፍ በሚያስችል መልኩ ምርቱን ለመጨመር ከክልል አመራሮቹ ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል።
በቀጣይም ዘርፉን ዘመናዊ መልክ ለማስያዝ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
የማዕድን ፈቃድ ተሰጥቷቸው በአግባቡ እየተጠቀሙበት ያልሆኑ ተቋማት ላይ መወሰድ ስላለበት እርምጃ በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።

Leave A Comment

MoM