የኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ

የኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ እና 61ኛ የቦርድ ስብሰባውን ከባለድርሻ አካላት ጋር በሃያት ሬጀንሲ አካሄዷል። በቦርድ ስብሰባው 5ኛ እና 6ኛ የኢኒሼቲቩ ሪፖርት ያለበት ደረጃ የቀረበ ሲሆን በዘርፉ የባለድርሻ አካላት አስተዋፆን ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል። መንግስት ፖለቲካዊ አመራር እና ድጋፍ መስጠት፣ ህግን ማውጣትና መከታተል ይኖርበታል ።
የማዕድን ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ህጋዊነታቸውን ማረጋገጥ፣ ግዴታቸውን መወጣት፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ግጭት አልባ ተግባቦት በመፍጠር ማልማት ይገባል ተብሏል። ሲቪክ ሶሳይቲም በማዕድን ኩባንያዎች አካባቢ የሚስተዋሉትን ችግሮች በመለየት እልባት እንዲበጅለት ማድረግ እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል። በመሆኑም በዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት ኢኒሼቲቩን ትኩረት በመስጠት መደገፍ እና ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አፅኖት ተሰጥቶበታል።
የኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ የ2013 ዓ.ም ቦርድ ስብሰባ ቴክኒካል ኮሚቴን በማዋቀር ተጠናቋል።

Leave A Comment

MoM