ኢ/ ታከለ ኡማ በምዕራብ ወለጋ የሚገኘውን የባህላዊ ወርቅ አምራቾችን ጎበኙ

Biyya Warqee fi Bunaa, Biyya dhadhaa fi dammaa wallagga oolle har’a. Dargaggoon baayy’een oomisha warqee aadaadhaan oomishan dinagdeen of danda’uuf xaaraa jiran jajjaabeessuuf.

Dargaggoo baayy’eetu hojii jalqabaniii bu’aa argachuu ifaajaa jiru.

Nutis meeshaa oomisha warqee adaaf ta’u deegaruuf ni hojjenna.

Rakkoo idoo gurgurtaa warqee kan tures baankiiin daldalaa Itoophiyaa wiirtuu Gimbitti akka irraa bituuf damee bittaa warqee banneef.

——————————————————————————————–

በድንቅ ተፈጥሮ በተከበበችው፣ የወርቅ የቡና ፤የዳበረ የተፈጥሮ ፀጋ መገኛ በሆነችው ወለጋ ተገኝቻለው። ወል አጋ(ወለጋ) እንደስሟ ሁሉን በጋራ ሁሉን በአንድነት ይዛለች። ይህቺ ሁሉን በጋራ የያዘች ሁሉን በአንድነት ያሰባሰበችው ወለጋ ግን የስሟንና የታሪኳን ያህል ማደግ፣ የጸጋዎቿን ያህል መጠቀም አልቻለችም። ከወለጋ ፀጋዎች አንዱ የሆነው የወርቅ ሀብቷ በተገቢው መልኩ ድጋፍ እንዲያገኝና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል እንሰራለን።የአካባቢው ወጣቶችም ከዚህ ሀብት ኑሮአቸው የሚቀየሩበት እድልን ማግኘት ይኖርባቸዋል።በቆይታዬ በምዕራብ ወለጋ ባህላዊ መንገድ ወርቅ ለማምረት በሂደት ላይ ያሉ ወጣቶችን የሚያመርቱበትን አካባቢ ተመልክቻልሁ።

ወጣቶቹ ጥረታቸው የሚደነቅ ቢሆንም ድጋፍ ግን ያስፈልጋቸዋል። ስራቸውን አጠናክረው በሚቀጥሉበት መንገድ እና ከሀብቱ የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ በሚሆንበት መንገድ ዙሪያም ከነዋሪዎች ጋር ተወያይተናል። የወለጋ የወርቅም ይሁን የትኛውም ሀብት ባክኖ መቅረት የለበትም። ወጣቶቿም ይህ ሀብት እያለ ስራ ፍለጋ መንከራተት የለባቸውም።ይህን ታሪክ የምንቀይርበት ወቅት ደግሞ አሁን ነው!

Leave A Comment

MoM