Category: News

በማህበረሰብ ልማት ፈንድ የተሰራ ፕሮጀክት ተመረቀ::

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት አስመረቀ።የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እና የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፕሮጀክቱን መርቀው ከፍተውታል። የተመረቀው ፕሮጀክት በድሬዳዋ ከተማ ለ700 የገንደ ሪጌ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ 1.8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ፓዮኔር ከተባለ የሲሚንቶ ኩባንያ ነው።የማዕድን ኩባንያዎች ማዕድንን […]
Read More

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የዘርፍ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድና የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ውይይት እየተካሄደ ነው

በማዕድንና ነዳጅ ዘርፎች የማዕድን የምርት አቅርቦት በማሳደግ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እና የ2013 ዓ.ም የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት የተደረገው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ነው ፡፡ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሚኒስቴር መስሪያ […]
Read More

ባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶለር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኘ

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል። ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዘሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ፤ ወርቅ፣ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፓየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡ ወርቅን በተመለከተ በባህላዊ መንገድ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 2ሺህ 241 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል፡፡ በእቅድነት ተይዞ የነበረው 251 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ […]
Read More

ኢ/ር ታከለ ኡማ በሲዳማ ክልል በሎጌታ ወንዝ ዳር ወርቅ ለማውጣት በሂደት ላይ የሚገኘውን የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ተመልክተዋል

ኢ/ር ታከለ ኡማ በሲዳማ ክልል የገናሌ ወንዝ ገባር በሆነው በሎጌታ ወንዝ ዳር ወርቅ ለማውጣት በሂደት ላይ የሚገኘውን የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ተመልክተዋል። የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ካምፓኒ ከሁለት ወር በኋሏ ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገ ነው። ካምፓኒው በአካባቢው ተወላጆች እና ነዋሪዎች ባለቤትነት የሚመራ እና የሚበረታታ መሆኑንም ኢ/ር ታከለ ተናግረዋል። አካባቢው ከፍተኛ የመንገድና የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት በመሆኑ […]
Read More

ኢ/ር ታከለ ኡማ በአፋር ክልል የሚገኙ የማአድን ልማት ስራዎችን እየተመለከቱ ነው

ኢ/ር ታከለ ከአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጋር በመሆን የፖታሽ፣ ጨውና ብሮሚን ምርቶች ላይ እየተከናወኑ ያሉ የማአድን ልማቶችን ተመልክተዋል። ኢ/ር ታከለ አፍዴራ አካባቢ “ታናራሙ ኬሚካልስ” በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገባ የሚገኘው የብሮሚን ፋብሪካ የጎበኙ ሲሆን ፋብሪካው በ57 ሚሊየን ዶላር ወጪ እየተገነባ የሚገኝ ነው። ፋብሪካው “ሀይድሮጅን ብሮማይድ አሲድ” አዘጋጅቶ ለውጪ ገበያ የሚያቀርብ ይሆናል። ፋብሪካው በቅርብ […]
Read More
MoM