“ ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ የሚጠቀሙ ማንኛውም ትልልቅ መኪኖች (ትራክ) ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት የተከለከለ ነው “ – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ […]
ኢ/ር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ጊቤ ይባሬ ቀበሌ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል። SUN Mining and Trading Plc የተባለ ሃገር በቀል ኩባንያ በ800 ሚሊዮን ብር የስራ ካፒታል የመደበ ሲሆን ለ1500 ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ የስራ እድል ይፈጥራል።በ10 ወራት ውስጥ የፋብሪካ ተከላው የሚያጠናቅቅ ሲሆን በሰአት 150 ቶን የድንጋይ ከሰል ያጥባል።ኩባንያው […]
ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር የ10 ወራትን አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በገቡት የስራ ውል መሰረት ወደ ስራ ያልገቡ የምርትና የምርመራ ፈቃዶችን ውላቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት አላቂ የሆነው የማዕድን […]
በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ካሉት 97 የምርመራ ፈቃዶች ለ27 በእቅዳቸው መሰረት መስራት ባለመቻላቸው ውላቸው ሲቋረጥ ለ3 ፈቃዶች ደግሞ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ለቀንጢቻ ታንታለም እና ለቱሊካፒ የወርቅ ኩባንያዎች በውላቸው መሠረት እንዲሠሩ በልዩ ሁኔታ የጊዜ ገደብ የተሠጣቸው ሲሆን በአግባቡ ካልሠሩ አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሠድ ይሆናል ተብሏል።ባለፉት 10 ወራትም ከዘርፉ 513.92 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ ንግድ ገቢ ማግኘት ተችሏል።
በማዕድንና ነዳጅ ዘርፎች የማዕድን የምርት አቅርቦት በማሳደግ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እና የ2013 ዓ.ም የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት የተደረገው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ነው ፡፡ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሚኒስቴር መስሪያ […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እና የስራ ሃላፊዎች የጌጣጌጥ ማዕድን ላኪዎችን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል::
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ኮርፓሬሽን የቦርድ አባላት ጋር በጋራ በመሆን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎብኝተዋል። ፋብሪካው ያለበት ቦታ ለሲሚንቶ ግብአት መሆን የሚችል የተፈጥሮ ሀብት በብዛት የሚገኝበት ቢሆንም ፋብሪካው የሚያመርተው ምርት ግን ይህንን የሚመጥን አለመሆኑን ተመልክተዋል።ፋብሪካው ሙሉ አቅሙ እንዲጠቀምና የሲሚንቶ አቅርቦቱ እንዲጨምር የምንሰራ ይሆናል ብለዋል ኢ/ር ታከለ:: የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በሲሚንቶ ገበያው ላይ ላይ ያለው ተሳትፎ […]