በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የከሰል ድንጋይ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

ኢ/ር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ጊቤ ይባሬ ቀበሌ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

Goal

SUN Mining and Trading Plc የተባለ ሃገር በቀል ኩባንያ በ800 ሚሊዮን ብር የስራ ካፒታል የመደበ ሲሆን ለ1500 ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ የስራ እድል ይፈጥራል።በ10 ወራት ውስጥ የፋብሪካ ተከላው የሚያጠናቅቅ ሲሆን በሰአት 150 ቶን የድንጋይ ከሰል ያጥባል።ኩባንያው ወደ ስራ ሲገባ ከውጪ የሚገባውን 1.2 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል ያስቀራል።አገሪቱ ለድንጋይ ከሰል የምታወጣውን 275 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያስቀራል።

Leave A Comment

MoM