ለባህላዊ፣ለልዩ አነስተኛ እና ለክልሎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጠ፡፡

በ2013 ዓ.ም በ10 ወራት ውስጥ በወርቅ የወጪ ንግድ ከ553 ሚሊየን ዶላር በላይ ማግኘት ገቢ ተገኝቷል፡፡ከሁለት አመት በፊት በ2011 ዓ.ም የወርቅ ገበያው በእጅጉ አሽቆልቁሎ 29 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ብቻ የተገኘ ሲሆን÷አሁን ላይ ሚኒስቴሩ በሰራው የለውጥ ስራ ገቢውን በእጅጉ ከፍ ማድረግ መቻሉ ተጠቁሟል።

በ2012 ዓ.ም ከ198ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን÷ በ2013 በ10 ወር ውስጥ 553ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል።

በዛሬው እለትም ለዚሁ ውጤት መገኘት ከወርቅ ማውጣት ጀምሮ በሁሉም እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ በወርቅ ምርት ላይ የተሰማሩና የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ ወርቅ በባህላዊ መንገድ መመረት የጀመረ ከ2000 አመታት በፊት እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።ለወርቅ ምርትና ንግድ ለዚህ መድረስ ባህላዊ አምራቾች ሰፊውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በባህላዊ የወርቅ ምርት ላይ የተሰማሩ ከ1ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይገኛሉ።የአመቱ ለውጪ ገበያ ከሚቀርበው የወርቅ ምርት ከ60 በመቶ በላይ ድርሻን የሚይዘው የወርቅ ምርት በባህላዊ መንገድ የሚመረት ነው።የትግራይ፣ የደቡብ፣ የኦሮሚያ፣ የጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉሙዝ በኢትዮጵያ በዚሁ መንገድ ወርቅ በማምረት የሚታወቁ አካባቢዎች ናቸው፡፡

Leave A Comment

MoM