ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ኮርፓሬሽን የቦርድ አባላት ጋር በጋራ በመሆን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎብኝተዋል። ፋብሪካው ያለበት ቦታ ለሲሚንቶ ግብአት መሆን የሚችል የተፈጥሮ ሀብት በብዛት የሚገኝበት ቢሆንም ፋብሪካው የሚያመርተው ምርት ግን ይህንን የሚመጥን አለመሆኑን ተመልክተዋል።ፋብሪካው ሙሉ አቅሙ እንዲጠቀምና የሲሚንቶ አቅርቦቱ እንዲጨምር የምንሰራ ይሆናል ብለዋል ኢ/ር ታከለ:: የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በሲሚንቶ ገበያው ላይ ላይ ያለው ተሳትፎ […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት በ2013 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ትግባራት ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎችና ከህዝብ ተወካዮች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ኮሚቴ አባላት ጋር ገምግሟል፡፡ የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡ ገቢው የተገኘው ከ4112 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ፣26.97 ቶን ታንታለም፣1625 ኪሎግራም ጥሬ […]
ኢ/ር ታከለ ኡማ በማአድንና ነዳጅ ዘርፍ እምቅ ሀብት የተለዩ ቦታዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን በተመለከተ ለረጅም ጊዜያት የተጠኑ ጥናቶችን በጋራ በማደራጀት ለምርት ዝግጁ የሆኑ ቦታዎች መለየታቸውም ተገልጿል።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል። ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዘሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ፤ ወርቅ፣ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፓየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡ ወርቅን በተመለከተ በባህላዊ መንገድ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 2ሺህ 241 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል፡፡ በእቅድነት ተይዞ የነበረው 251 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ […]
ኢ/ር ታከለ ኡማ በሲዳማ ክልል የገናሌ ወንዝ ገባር በሆነው በሎጌታ ወንዝ ዳር ወርቅ ለማውጣት በሂደት ላይ የሚገኘውን የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ተመልክተዋል። የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ካምፓኒ ከሁለት ወር በኋሏ ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገ ነው። ካምፓኒው በአካባቢው ተወላጆች እና ነዋሪዎች ባለቤትነት የሚመራ እና የሚበረታታ መሆኑንም ኢ/ር ታከለ ተናግረዋል። አካባቢው ከፍተኛ የመንገድና የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት በመሆኑ […]
ኢ/ር ታከለ ኡማ በቤኔሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኙ የማዕድን ማውጫ ቦታዎችን ከክልሉ ርዕሰመስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን ተመልክተዋል። አሻሽሬ አካባቢ ወርቅ በማውጣት ሂደት ላይ የሚገኘውን “አስኮም ማይኒንግ” ከተመለከቷቸው ቦታዎች አንዱ ነው። ካምፓኒው በአካባቢው ወርቅ እና የከበሩ ማዕድናትን በማፈላለግ ሂደት ላይ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ወደ ምርት ለመግባት የሚያስችለውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል። ሚንስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ […]
ኢ/ር ታከለ ከአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጋር በመሆን የፖታሽ፣ ጨውና ብሮሚን ምርቶች ላይ እየተከናወኑ ያሉ የማአድን ልማቶችን ተመልክተዋል። ኢ/ር ታከለ አፍዴራ አካባቢ “ታናራሙ ኬሚካልስ” በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገባ የሚገኘው የብሮሚን ፋብሪካ የጎበኙ ሲሆን ፋብሪካው በ57 ሚሊየን ዶላር ወጪ እየተገነባ የሚገኝ ነው። ፋብሪካው “ሀይድሮጅን ብሮማይድ አሲድ” አዘጋጅቶ ለውጪ ገበያ የሚያቀርብ ይሆናል። ፋብሪካው በቅርብ […]
አዲስ እየተዘጋጀ ባለው የማአድንና ነዳጅ ፖሊሲ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። በውይይቱ ላይ ሚኒስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተገኝተዋል። በማአድንና ነዳጅ ዘርፍ እስካሁን ፖሊሲ ያልነበረ ሲሆን ዘረፉ በአዋጅና መመሪያዎች የሚመራ ነበር። በፖሊሲ ውይይቱ ላይ የማይክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ቡድን አባላትና በዘርፉ ረጅም አመት ልምድ ያላቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ከዚህ ውይይት በኋላ ፖሊሲው ላይ ከውይይቱ የተገኙ ግብአቶች ተጨምረውበት […]
የስልጠናውን አላማ አስመልከተው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ዶ/ር ኳንግ ቱትላም እንደገለጹት የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልል ማዕድን ቢሮዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች በነዳጅ ማደያዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርጉ ውክልና የሰጣቸው ሲሆን የባለሙያዎችን አቅም በመገንባት በዘረፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅርፍ ስልጠናው […]