የድንጋይ ከሰልን በሀገር ውስጥ ለማምረት ላሰብነው ሀሳብ ሁለተኛውን እርምጃ ተራምደናል። በዛሬው እለትም ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን በአሶሳ ሁለተኛውን የከሰል ድንጋይ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ አስጀምረናል ። ፋብሪካውን NOC የሚያስገነባውና በ11 ወራት የሚጠናቀቅ ይሆናል። በቀጣይ ቀናትም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ተጨማሪ የድንጋይ ከሰል ማምረቻዎችን ግንባታ እናስጀምራለን። 

ፋብሪካዎቹ ማምረት ሲጀምሩ ሀገራዊ የማምረት አቅማችን በአመት 2.5 ሚሊዮን ቶን እሴት የተጨመረበት ( blending , washing and scrubing coal) የድንጋይ ከሰል ይሆናል።ይህ ምርት በውጪ ምንዛሪ ከውጪ የምናስገባውን የድንጋይ ከሰል በተሻለ ሁኔታ ማስቀረት የሚችል ነው።
