ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር የ10 ወራትን አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በገቡት የስራ ውል መሰረት ወደ ስራ ያልገቡ የምርትና የምርመራ ፈቃዶችን ውላቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት አላቂ የሆነው የማዕድን […]
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ለክልል የማዕድን ፈቃድ ባለሙያዎች የካዳስተር አጠቃቀም ስልጠና ሰጠ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማዕድን ፈቃድን ለማስተዳደር ካዳስተር በመጠቀም ለባለፈቃዶች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ አገልግሎቱ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ በሁሉም ክልሎች ወጥ የሆነ የፈቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር እንዲኖር ለማስቻል ከክልል ለተውጣጡ የዘርፉ ባሙያዎች ለአንድ ሳምንት ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ካዳስተር ፈቃድ የተሰጠባቸው እና ያልተሠጠባቸውን ቦታዎች በቀላሉ መለየት ያስችላል፡፡ […]