የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

የኢፌዴሪ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች “ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ለሀገር መከላከያ ሠራዊትም ደም ለግሰዋል፡፡ የህወኃት ጁንታ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል፡፡ ህግ ለማስከበር ለተሰማራው ሃይል ደም በመለገስ የአጋርነት ድጋፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በቀጣይም ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ስመኝ ውቤ የህወኃት ጁንታ ቡድን በሰሜን እዝ ላይ ያደረሰው ጥቃት እጅግ አሳፋሪ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ በደም ልገሳ የጀመረው ድጋፍ በቀጣይ ለመከላከያ ሰራዊ የሚደረገው ድጋፋ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ በዕለቱም ለደም ለጋሾች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡

Leave A Comment

MoM