በጉብኝቱ ላይም የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጉብኝቱን አስመልክቶ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃም፥ “በሶማሌ ክልል ሂላላ እና ካሉብ የነዳጅ ማውጣት የሚያካሄድበትን ቦታ ተመልክቻለሁ” ብለዋል።
የነዳጅ ማውጣት ስራው መጠነኛ እንቅፋቶች ቢኖሩም ስራውን በነበረበት ፍጥነት ለማስቀጠል ፕሮጀክቱን ከሚያከናውነው ተቋምና ከክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ጋር መወያየታቸውንም አስታውቀዋል።
የተወያዩበት ጉዳይም በቅርቡ ውጤቱ በተግባር የሚታይ መሆኑንም የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።
“የህዝባችን ጥቅም አስጠብቀን የተፈጥሮ ፀጋችንን ሀብት የማድረግ ጥረታችን ይቀጥላል” ሲሉም ገልፀዋል።