የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በነዳጅ ጥራትና ደህንነት ላይ ለክልል ማዕድን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ

የስልጠናውን አላማ አስመልከተው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ዶ/ር ኳንግ ቱትላም እንደገለጹት የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልል ማዕድን ቢሮዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች በነዳጅ ማደያዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርጉ ውክልና የሰጣቸው ሲሆን የባለሙያዎችን አቅም በመገንባት በዘረፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅርፍ ስልጠናው ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከአንድ ሽህ ሁለት መቶ በላይ ማደያዎች ያሉ ሲሆን ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነ የነዳጅ ተቋማት ደረጃ ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ ጥላሁን ሞገስ ተናገረዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የነዳጅ ውጤቶች ፍተሻ አሰራር፣የክትትልና ቁጥጥር እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ላይ ያገኙትን የተግባር ስልጠና ተግባራዊ በማደረግ ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ የነዳጅ ስርጭት እንዲኖር የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

Leave A Comment

MoM