News and Events

 

የአነስተኛ ደረጃ የደለል ወርቅ ማዕድን ማምረት ፈቃድ ተሰጠ

የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ናንካይ ማይኒንግ ሃላፊነቱ የተወሰነየግል ማህበር ለተባለ የቻይና ኩባንያ የአነስተኛ ደረጃደለል ወርቅ ማዕድን ማምረት ፈቃድ ሰጠ፡፡

ስምምነቱን በፈቃድ ሰጪው መ/ቤት በኩል የፈረሙት ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳየማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሲሆኑ በባለፈቃዱ በኩል ደግሞ ሚስተር ኬሺንካ  የኩባንያውዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡

የውሉ ስምምነት ፊርማው ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ለ2 /ለሁለት / ዓመታትየሚፀና ሆኖ የፈቃድ ዘመኑም ሲጠናቀቅ በባለፈቃዱ ጥያቄ መሠረት በእያንዳንዱ የፈቃድ ዕድሳት ጊዜ ከ5/ ከአምስት / ዓመታት ላልበለጠግዜ ሊታደስ ይችላል፡፡

ኩባንያው ፈቃድ ያገኘው በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ አኝዋክ ዞን ፣ አበቦ ወረዳ ሲሪ ወንዝ አካባቢ የሚገኝሲሆን የቆዳ ስፋም 2.04 ካሬኪሎሜትር የሚሸፍን ነው፡፡

ኩባንያው ለኢንቨስትመንት ወጪ 50,302,000.00 (ሀምሳ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሁለት ሺ ብር / መድቧል፡፡ ኩባንያውወደ ሥራ ሲገባ ለ57 ኢትዮጵያዊያን የሥራ ዕድል የሚፈጥር ሲሆንበ2 አመታት ውስጥ 210 ኪ.ግ የደለል ወርቅ ያመርታል፡፡

ባለፈቃዱየምርት ሥራውን ሲያከናውን በፌደራልና በክልል የማዕድን አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን መሰረት አድርጎ በጥንቃቄ በትጋትና ቅልጥፍናበተሞላበት ሁኔታ በማዕድን ኢንዱስትሪው ዘርፍ ተቀባይነት ባለው የአሰራር ዘዴ ለማከናወን ስምምነቱ ፊርማ ውስጥ የተካተተ ሲሆን ተመጣጣኝዕውቀት፣ ችሎታና ልምድ ላላቸው ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ቅድሚያ የስራ ዕድል ለመስጠትና ለስራው አስፈላጊ የሆነውን ሥልጠና ለመስጠት ግዴታ ገብቷል፡፡

የአካካቢጥበቃን በተመለከተ የሠራተኞቹን፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጤንነትና ደህንነት በማይጎዳና ብክለት በማያስከትል መልኩ የምርት ስራውንለማከናወን ውል የፈፀመ ሲሆን ሥራውን ሲያቋርጥ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ፣ በሰው ህይወትና ንብረት እንዲሁም ዕፅዋት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ማናቸውም ቅሪቶችና ግንባታዎችን ያስወግዳል፡፡