ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር የ10 ወራትን አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በገቡት የስራ ውል መሰረት ወደ ስራ ያልገቡ የምርትና የምርመራ ፈቃዶችን ውላቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት አላቂ የሆነው የማዕድን ሃብት በአግባቡ ከተመራና ማልማት ከተቻለ ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችል ባለፉት 10 ወራት የተመዘገበው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማሳያ ነው። ዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ግኝት በማስገኘት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የብዙዎችን ሕይወት እየቀየረ ይገኛል፡፡
ባለፉት ወራት ከወርቅ ብቻ 504 ሚሊዮን በላይ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ ተገኝቷል፡፡ ዘርፉ ለ93,599 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡
የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ የተሰሩት ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ያሏቸው ሃሳቦችን አንስተዋል፡፡