“ምርታችን የተፈጥሮ ሀብታችንን የሚመጥን መሆን ይገባዋል።”- ኢ/ር ታከለ ኡማ

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ኮርፓሬሽን የቦርድ አባላት ጋር በጋራ በመሆን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

ፋብሪካው ያለበት ቦታ ለሲሚንቶ ግብአት መሆን የሚችል የተፈጥሮ ሀብት በብዛት የሚገኝበት ቢሆንም ፋብሪካው የሚያመርተው ምርት ግን  ይህንን የሚመጥን አለመሆኑን ተመልክተዋል።ፋብሪካው ሙሉ አቅሙ እንዲጠቀምና የሲሚንቶ አቅርቦቱ እንዲጨምር የምንሰራ ይሆናል ብለዋል ኢ/ር ታከለ::

የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በሲሚንቶ ገበያው ላይ ላይ ያለው ተሳትፎ 25በመቶ ብቻ ነው።የፋብሪካውን ምርትና ተደራሽነት በማስፋትም ይህ የገበያ ድርሻ ከፍ እንዲል ድጋፍ እናደርጋለን ያሉት ኢ/ር ታከለ ሌላው በትኩረት የምንሰራበት ጉዳይ የገበያ ትስስሩን ማጠንከር ላይ ይሆናልም ብለዋል። ፋብሪካው የሚያመርተውን ምርት በዝቅተኛ ዋጋ የሚያቀርብ ቢሆንም ገበያ ላይ በእጥፍ እየተሸጠ ይገኛል። ይህንን ማስተካከልም ትልቁ ስራችን ይሆናል።በአጠቃላይም ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን ታሪኩንና አቅሙን በሚመጥን መልኩ ለማሳደግ እንሰራለን ብለዋል።

Leave A Comment