ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት በ2013 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ትግባራት ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎችና ከህዝብ ተወካዮች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ኮሚቴ አባላት ጋር ገምግሟል፡፡
የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡ ገቢው የተገኘው ከ4112 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ፣26.97 ቶን ታንታለም፣1625 ኪሎግራም ጥሬ ኦፓል 37.8 ኪ.ግ እሴት የተጨመረበት ኦፓል እና 2123ኪ.ግ ሌሎች የጌጣጌጥ ማዕድናት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተችሏል፡፡ ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡ የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን ማዕድናት 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡
በዘርፉ ለ48,785 ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎችና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የቀጣይ ስድስት ወራት የዕቅድ አቅጣጫዎች ተቀምጧል፡፡

Leave A Comment