“በማአድን ዘርፉ ቀጣይ ትኩረት ሀገራዊ ፍላጎት ላይ ማተኮርና የውጪውን ገበያ ማሳደግ ላይ ይሆናል” ኢ/ር ታከለ ኡማ

ኢ/ር ታከለ ኡማ በማአድንና ነዳጅ ዘርፍ እምቅ ሀብት የተለዩ ቦታዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን በተመለከተ ለረጅም ጊዜያት የተጠኑ ጥናቶችን በጋራ በማደራጀት ለምርት ዝግጁ የሆኑ ቦታዎች መለየታቸውም ተገልጿል።

የተዘጋጁት ቦታዎች ስራቸውን በተገቢው መንገድ ባለማከናወናቸው ፍቃዳቸው ከተሰረዙ ተቋማት የተነጠቁ ቦታዎች የተካተቱበት ነው።

በቀጣይ ጊዚያት ቦታዎቹ ለሀገር ውስጥና ለአለም አቀፍ ተቋማት ክፍት እንደሚሆኑ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

ቦታዎቹን ወደስራ ለማስገባትም በቅርብ ገዜያት አለም አቀፍ ጨረታ የሚወጣ ይሆናል።

ኢ/ር ታከለ ኡማ የማአድን ዘርፉ ቀጣይ ትኩረት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን መነሻ ባደረገ መልኩ የውጪ ምንዛሪ ገቢን ማሳደግ ይሆናል ብለዋል።

ይህም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር የተናበበ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።

ኢ/ር ታከለ ኡማ ኢትዮጵያ ያሏትን የማአድንና ነዳጅ ሀብቶች በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንትን በመሳብ መገናኛ ብዙሀን ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave A Comment